ማቴዎስ 13:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 አንድ ሰው የመንግሥቱን ቃል ሰምቶ የማያስተውል ከሆነ ክፉው+ መጥቶ በልቡ ውስጥ የተዘራውን ዘር ይነጥቀዋል፤ በመንገድ ዳር የተዘራው ዘር ይህ ነው።+ ማርቆስ 4:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ቃሉ ሲዘራ መንገድ ዳር እንደወደቁት ዘሮች የሆኑት እነዚህ ናቸው፤ ቃሉን እንደሰሙ ግን ሰይጣን መጥቶ+ በውስጣቸው የተዘራውን ቃል ይወስደዋል።+ 2 ቆሮንቶስ 4:3, 4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 እንግዲህ የምናውጀው ምሥራች በእርግጥ የተሸፈነ ከሆነ የተሸፈነው ወደ ጥፋት እያመሩ ላሉት ነው፤ 4 የአምላክ አምሳል ስለሆነው ስለ ክርስቶስ+ የሚገልጸውና ክብራማ የሆነው ምሥራች የሚፈነጥቀው ብርሃን በእነሱ ላይ እንዳያበራ+ የዚህ ሥርዓት* አምላክ+ የማያምኑትን ሰዎች አእምሮ አሳውሯል።+
3 እንግዲህ የምናውጀው ምሥራች በእርግጥ የተሸፈነ ከሆነ የተሸፈነው ወደ ጥፋት እያመሩ ላሉት ነው፤ 4 የአምላክ አምሳል ስለሆነው ስለ ክርስቶስ+ የሚገልጸውና ክብራማ የሆነው ምሥራች የሚፈነጥቀው ብርሃን በእነሱ ላይ እንዳያበራ+ የዚህ ሥርዓት* አምላክ+ የማያምኑትን ሰዎች አእምሮ አሳውሯል።+