ማቴዎስ 10:34-36 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 በምድር ላይ ሰላም ለማስፈን የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ የመጣሁት ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አይደለም።+ 35 እኔ የመጣሁት ወንድ ልጅን ከአባቱ፣ ሴት ልጅን ከእናቷ እንዲሁም ምራትን ከአማቷ ለመለያየት ነው።+ 36 በእርግጥም የሰው ጠላቶቹ የገዛ ቤተሰቦቹ ይሆናሉ። ዮሐንስ 7:41 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 41 ሌሎችም “ይህ ክርስቶስ ነው”+ ይሉ ነበር። አንዳንዶች ግን እንዲህ አሉ፦ “ክርስቶስ የሚመጣው ከገሊላ ነው እንዴ?+ ዮሐንስ 7:43 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 43 ስለዚህ እሱን በተመለከተ በሕዝቡ መካከል ክፍፍል ተፈጠረ። ዮሐንስ 9:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ከፈሪሳውያንም መካከል አንዳንዶቹ “ይህ ሰው ሰንበትን ስለማያከብር ከአምላክ የመጣ አይደለም” አሉ።+ ሌሎቹ ደግሞ “ኃጢአተኛ የሆነ ሰው እንዲህ ያሉ ተአምራዊ ምልክቶችን እንዴት ሊፈጽም ይችላል?” አሉ።+ በመሆኑም በመካከላቸው ክፍፍል ተፈጠረ።+
34 በምድር ላይ ሰላም ለማስፈን የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ የመጣሁት ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አይደለም።+ 35 እኔ የመጣሁት ወንድ ልጅን ከአባቱ፣ ሴት ልጅን ከእናቷ እንዲሁም ምራትን ከአማቷ ለመለያየት ነው።+ 36 በእርግጥም የሰው ጠላቶቹ የገዛ ቤተሰቦቹ ይሆናሉ።
16 ከፈሪሳውያንም መካከል አንዳንዶቹ “ይህ ሰው ሰንበትን ስለማያከብር ከአምላክ የመጣ አይደለም” አሉ።+ ሌሎቹ ደግሞ “ኃጢአተኛ የሆነ ሰው እንዲህ ያሉ ተአምራዊ ምልክቶችን እንዴት ሊፈጽም ይችላል?” አሉ።+ በመሆኑም በመካከላቸው ክፍፍል ተፈጠረ።+