ማቴዎስ 10:37 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 37 ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ሁሉ ለእኔ ሊሆን አይገባም፤ ከእኔ ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ሁሉ ለእኔ ሊሆን አይገባም።+ ሉቃስ 18:29, 30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ለአምላክ መንግሥት ሲል ቤትን ወይም ሚስትን ወይም ወንድሞችን ወይም ወላጆችን ወይም ልጆችን የተወ ሁሉ፣+ 30 አሁን በዚህ ዘመን ብዙ እጥፍ፣ በሚመጣው ሥርዓት* ደግሞ የዘላለም ሕይወት ያገኛል።”+ ዮሐንስ 12:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 ሕይወቱን የሚወድ ሁሉ* ያጠፋታል፤ በዚህ ዓለም ሕይወቱን* የሚጠላ+ ሁሉ ግን ለዘላለም ሕይወት ይጠብቃታል።+
29 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ለአምላክ መንግሥት ሲል ቤትን ወይም ሚስትን ወይም ወንድሞችን ወይም ወላጆችን ወይም ልጆችን የተወ ሁሉ፣+ 30 አሁን በዚህ ዘመን ብዙ እጥፍ፣ በሚመጣው ሥርዓት* ደግሞ የዘላለም ሕይወት ያገኛል።”+