-
ማቴዎስ 16:21አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
21 ከዚያን ጊዜ አንስቶ፣ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም መሄድ እንዳለበት እንዲሁም በሽማግሌዎች፣ በካህናት አለቆችና በጸሐፍት እጅ ከባድ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ እንደሚገባው ብሎም በሦስተኛው ቀን እንደሚነሳ ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጽላቸው ጀመር።+
-
-
ማርቆስ 10:32-34አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
32 ወደ ኢየሩሳሌም በሚወስደው መንገድ እያቀኑ ሳሉ ኢየሱስ ከፊት ከፊታቸው ይሄድ ነበር፤ እነሱም ተደነቁ፤ ይከተሉት የነበሩት ሰዎች ግን ፍርሃት አደረባቸው። እሱም እንደገና አሥራ ሁለቱን ገለል አድርጎ በመውሰድ የሚደርስበትን ነገር ይነግራቸው ጀመር፦+ 33 “እነሆ፣ ወደ ኢየሩሳሌም እየወጣን ነው፤ የሰው ልጅ ለካህናት አለቆችና ለጸሐፍት አልፎ ይሰጣል። እነሱም ሞት ይፈርዱበታል፤ ለአሕዛብም አሳልፈው ይሰጡታል፤ 34 ያፌዙበታል፤ ይተፉበታል፤ ይገርፉታል፤ ከዚያም ይገድሉታል፤ ሆኖም ከሦስት ቀን በኋላ ይነሳል።”+
-