የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማቴዎስ 26:14-16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 ከዚህ በኋላ፣ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ+ ወደ ካህናት አለቆች ሄዶ+ 15 “እሱን አሳልፌ ብሰጣችሁ ምን ትሰጡኛላችሁ?” አላቸው።+ እነሱም 30 የብር ሳንቲሞች* ሊሰጡት ተስማሙ።+ 16 ስለዚህ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ኢየሱስን አሳልፎ ለመስጠት ምቹ አጋጣሚ ይፈልግ ነበር።

  • ማርቆስ 14:10, 11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ ሊሰጠው ወደ ካህናት አለቆች ሄደ።+ 11 እነሱም ይህን ሲሰሙ ደስ አላቸውና የብር ገንዘብ* ሊሰጡት ቃል ገቡለት።+ ስለዚህ እሱን አሳልፎ የሚሰጥበትን አጋጣሚ ይፈልግ ጀመር።

  • ዮሐንስ 6:70
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 70 ኢየሱስም መልሶ “አሥራ ሁለታችሁንም የመረጥኳችሁ እኔ አይደለሁም?+ ይሁንና ከመካከላችሁ አንዱ ስም አጥፊ* ነው” አላቸው።+

  • ዮሐንስ 13:2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 2 በዚህ ጊዜ ራት እየበሉ ነበር። ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ ይሁዳ+ ልብ ውስጥ ኢየሱስን አሳልፎ የመስጠት ሐሳብ አሳድሮ ነበር።+

  • ዮሐንስ 13:27
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 27 ይሁዳም ቁራሹን ከተቀበለ በኋላ ሰይጣን ገባበት።+ ስለዚህ ኢየሱስ “እያደረግከው ያለኸውን ነገር ቶሎ አድርገው” አለው።

  • የሐዋርያት ሥራ 1:16, 17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 “ወንድሞች፣ ኢየሱስን የያዙትን ሰዎች እየመራ ስላመጣው ስለ ይሁዳ+ መንፈስ ቅዱስ በዳዊት በኩል በትንቢት የተናገረው የቅዱስ መጽሐፉ ቃል መፈጸሙ የግድ ነበር።+ 17 ምክንያቱም እሱ ከእኛ እንደ አንዱ ተቆጥሮ የነበረ+ ከመሆኑም በላይ በዚህ አገልግሎት የመካፈል አጋጣሚ አግኝቶ ነበር።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ