ኢሳይያስ 52:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 እናንተ የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች፣ ደስ ይበላችሁ፤ በአንድነትም እልል በሉ፤+ይሖዋ ሕዝቡን አጽናንቷልና፤+ ኢየሩሳሌምንም ተቤዥቷል።+ ማርቆስ 15:43 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 43 የተከበረ የሸንጎ* አባል የሆነውና የአምላክን መንግሥት ይጠባበቅ የነበረው የአርማትያሱ ዮሴፍ መጣ። ደፍሮም ወደ ጲላጦስ ገባና የኢየሱስ አስከሬን እንዲሰጠው ጠየቀ።+ ሉቃስ 2:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 እነሆም፣ በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ እሱም አምላክ እስራኤልን የሚያጽናናበትን+ ጊዜ የሚጠባበቅ ጻድቅና ለአምላክ ያደረ ሰው ነበር፤ መንፈስ ቅዱስም በእሱ ላይ ነበር።
43 የተከበረ የሸንጎ* አባል የሆነውና የአምላክን መንግሥት ይጠባበቅ የነበረው የአርማትያሱ ዮሴፍ መጣ። ደፍሮም ወደ ጲላጦስ ገባና የኢየሱስ አስከሬን እንዲሰጠው ጠየቀ።+
25 እነሆም፣ በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ እሱም አምላክ እስራኤልን የሚያጽናናበትን+ ጊዜ የሚጠባበቅ ጻድቅና ለአምላክ ያደረ ሰው ነበር፤ መንፈስ ቅዱስም በእሱ ላይ ነበር።