ዮሐንስ 5:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 በራሴ ተነሳስቼ አንድም ነገር ማድረግ አልችልም። እንደሰማሁ እፈርዳለሁ፤ የራሴን ፈቃድ ሳይሆን የላከኝን ፈቃድ+ መፈጸም ስለምፈልግ የምፈርደው የጽድቅ ፍርድ ነው።+ ዮሐንስ 5:36 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 36 እኔ ግን ከዮሐንስ የበለጠ ምሥክር አለኝ፤ ምክንያቱም አባቴ እንዳከናውነው የሰጠኝ ሥራ ማለትም እየሠራሁት ያለው ይህ ሥራ አብ እንደላከኝ ይመሠክራል።+ ዮሐንስ 17:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 እንድሠራው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ+ በምድር ላይ አከበርኩህ።+ ዮሐንስ 19:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 ኢየሱስ የኮመጠጠውን ወይን ጠጅ ከቀመሰ በኋላ “ተፈጸመ!”+ አለ፤ ራሱንም ዘንበል አድርጎ መንፈሱን ሰጠ።*+
30 በራሴ ተነሳስቼ አንድም ነገር ማድረግ አልችልም። እንደሰማሁ እፈርዳለሁ፤ የራሴን ፈቃድ ሳይሆን የላከኝን ፈቃድ+ መፈጸም ስለምፈልግ የምፈርደው የጽድቅ ፍርድ ነው።+