ማቴዎስ 14:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ኢየሱስ ይህን ሲሰማ ብቻውን ለመሆን በጀልባ ተሳፍሮ ገለል ወዳለ ስፍራ ሄደ። ሕዝቡ ግን መሄዱን ሰምተው ከየከተማው እየወጡ በእግር ተከተሉት።+ ሉቃስ 9:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ሐዋርያቱም በተመለሱ ጊዜ ያደረጉትን ነገር ሁሉ ለኢየሱስ ተረኩለት።+ እሱም ቤተሳይዳ ወደምትባል ከተማ ብቻቸውን ይዟቸው ሄደ።+