2 ማርያም በጌታ ላይ ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት ያፈሰሰችውና በፀጉሯ እግሩን ያበሰችው+ ሴት ስትሆን የታመመውም፣ ወንድሟ አልዓዛር ነበር። 3 ስለዚህ እህቶቹ “ጌታ ሆይ፣ የምትወደው ሰው ታሟል” ሲሉ መልእክት ላኩበት። 4 ኢየሱስ ግን ይህን በሰማ ጊዜ “ይህ ሕመም ለአምላክ ክብር የሚያመጣ ነው+ እንጂ በሞት የሚያበቃ አይደለም፤ ይህም የአምላክ ልጅ በዚህ አማካኝነት ክብር ይጎናጸፍ ዘንድ ነው” አለ።