ዮሐንስ 3:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ይህ ሰው በማታ ወደ ኢየሱስ መጥቶ+ እንዲህ አለው፦ “ረቢ፣+ አንተ ከአምላክ ዘንድ የመጣህ አስተማሪ እንደሆንክ እናውቃለን፤ ምክንያቱም አምላክ ከእሱ ጋር ካልሆነ በቀር+ አንተ የምትፈጽማቸውን ተአምራዊ ምልክቶች መፈጸም የሚችል አንድም ሰው የለም።”+ ዮሐንስ 5:36 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 36 እኔ ግን ከዮሐንስ የበለጠ ምሥክር አለኝ፤ ምክንያቱም አባቴ እንዳከናውነው የሰጠኝ ሥራ ማለትም እየሠራሁት ያለው ይህ ሥራ አብ እንደላከኝ ይመሠክራል።+ ዮሐንስ 10:38 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 38 የአባቴን ሥራ እየሠራሁ ከሆነ ግን እኔን ባታምኑኝ እንኳ ሥራዬን እመኑ፤+ ይህም አብ ከእኔ ጋር አንድነት እንዳለው እንዲሁም እኔም ከአብ ጋር አንድነት እንዳለኝ እንድታውቁና ይህን ይበልጥ እያወቃችሁ እንድትሄዱ ነው።”+ ዮሐንስ 14:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 እኔ ከአብ ጋር አንድነት እንዳለኝና አብ ከእኔ ጋር አንድነት እንዳለው አታምንም?+ የምነግራችሁን ነገር የምናገረው ከራሴ አመንጭቼ አይደለም፤+ ሆኖም ሥራውን እየሠራ ያለው ከእኔ ጋር አንድነት ያለው አብ ነው። የሐዋርያት ሥራ 2:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ ይህን ቃል ስሙ፦ እናንተ ራሳችሁ እንደምታውቁት፣ አምላክ በኢየሱስ አማካኝነት በመካከላችሁ የፈጸማቸው ተአምራት፣ ድንቅ ነገሮችና ምልክቶች የናዝሬቱ ኢየሱስ በአምላክ የተላከ ሰው እንደሆነ የሚያሳዩ ማስረጃዎች ናቸው።+
2 ይህ ሰው በማታ ወደ ኢየሱስ መጥቶ+ እንዲህ አለው፦ “ረቢ፣+ አንተ ከአምላክ ዘንድ የመጣህ አስተማሪ እንደሆንክ እናውቃለን፤ ምክንያቱም አምላክ ከእሱ ጋር ካልሆነ በቀር+ አንተ የምትፈጽማቸውን ተአምራዊ ምልክቶች መፈጸም የሚችል አንድም ሰው የለም።”+
38 የአባቴን ሥራ እየሠራሁ ከሆነ ግን እኔን ባታምኑኝ እንኳ ሥራዬን እመኑ፤+ ይህም አብ ከእኔ ጋር አንድነት እንዳለው እንዲሁም እኔም ከአብ ጋር አንድነት እንዳለኝ እንድታውቁና ይህን ይበልጥ እያወቃችሁ እንድትሄዱ ነው።”+
10 እኔ ከአብ ጋር አንድነት እንዳለኝና አብ ከእኔ ጋር አንድነት እንዳለው አታምንም?+ የምነግራችሁን ነገር የምናገረው ከራሴ አመንጭቼ አይደለም፤+ ሆኖም ሥራውን እየሠራ ያለው ከእኔ ጋር አንድነት ያለው አብ ነው።
22 “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ ይህን ቃል ስሙ፦ እናንተ ራሳችሁ እንደምታውቁት፣ አምላክ በኢየሱስ አማካኝነት በመካከላችሁ የፈጸማቸው ተአምራት፣ ድንቅ ነገሮችና ምልክቶች የናዝሬቱ ኢየሱስ በአምላክ የተላከ ሰው እንደሆነ የሚያሳዩ ማስረጃዎች ናቸው።+