ማቴዎስ 3:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃው ወጣ፤ እነሆ፣ ሰማያት ተከፈቱ፤+ የአምላክም መንፈስ በእሱ ላይ እንደ ርግብ ሲወርድ አየ።+ ማርቆስ 1:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ወዲያው ከውኃው እንደወጣ ሰማያት ተከፍተው መንፈስ እንደ ርግብ በእሱ ላይ ሲወርድ አየ።+ ሉቃስ 3:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 መንፈስ ቅዱስም አካላዊ ቅርጽ ይዞ በርግብ መልክ በእሱ ላይ ወረደ፤ ከዚያም “አንተ የምወድህ ልጄ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል” የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ።+