ማቴዎስ 26:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ይህች ሴት ዘይቱን በሰውነቴ ላይ ስታፈስ እኔን ለቀብር ማዘጋጀቷ ነው።+ ማርቆስ 14:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 እሷ የምትችለውን አድርጋለች፤ ሰውነቴን ለቀብሬ ለማዘጋጀት ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት አስቀድማ ቀብታዋለች።+ ዮሐንስ 19:40 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 40 የኢየሱስንም አስከሬን ወስደው በአይሁዳውያን የአገናነዝ ልማድ መሠረት ጥሩ መዓዛ ባላቸው በእነዚህ ቅመሞች ተጠቅመው በበፍታ ጨርቅ ገነዙት።+