ዮሐንስ 5:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ስለሆነም ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ወልድ፣ አብ ሲያደርግ ያየውን ብቻ እንጂ በራሱ ተነሳስቶ አንድም ነገር ሊያደርግ አይችልም።+ አብ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድም በተመሳሳይ መንገድ ያንኑ ያደርጋል። ዮሐንስ 7:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “የማስተምረው ትምህርት የራሴ ሳይሆን ከላከኝ የመጣ ነው።+ ዮሐንስ 12:49 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 49 እኔ የተናገርኩት በራሴ ተነሳስቼ አይደለምና፤ ከዚህ ይልቅ ምን እንደምልና ምን እንደምናገር ያዘዘኝ የላከኝ አብ ራሱ ነው።+
19 ስለሆነም ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ወልድ፣ አብ ሲያደርግ ያየውን ብቻ እንጂ በራሱ ተነሳስቶ አንድም ነገር ሊያደርግ አይችልም።+ አብ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድም በተመሳሳይ መንገድ ያንኑ ያደርጋል።