ዮሐንስ 6:56 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 56 ሥጋዬን የሚበላና ደሜን የሚጠጣ ሁሉ ከእኔ ጋር አንድነት ይኖረዋል፤ እኔም ከእሱ ጋር አንድነት ይኖረኛል።+ 1 ቆሮንቶስ 12:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 እንግዲህ እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ፤+ እያንዳንዳችሁም በግለሰብ ደረጃ የአካሉ ክፍል ናችሁ።+ ኤፌሶን 4:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 በእሱ አማካኝነት የአካል ክፍሎች ሁሉ+ አስፈላጊ የሆነውን ነገር በሚያሟላው በእያንዳንዱ መገጣጠሚያ አማካኝነት እርስ በርስ ተስማምተው ተገጣጥመዋል። እያንዳንዱ የአካል ክፍል በአግባቡ ሥራውን ማከናወኑ አካሉ ራሱን በፍቅር እያነጸ እንዲያድግ አስተዋጽኦ ያበረክታል።+
16 በእሱ አማካኝነት የአካል ክፍሎች ሁሉ+ አስፈላጊ የሆነውን ነገር በሚያሟላው በእያንዳንዱ መገጣጠሚያ አማካኝነት እርስ በርስ ተስማምተው ተገጣጥመዋል። እያንዳንዱ የአካል ክፍል በአግባቡ ሥራውን ማከናወኑ አካሉ ራሱን በፍቅር እያነጸ እንዲያድግ አስተዋጽኦ ያበረክታል።+