ማቴዎስ 13:55 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 55 ይህ የአናጺው ልጅ አይደለም?+ እናቱስ ማርያም አይደለችም? ወንድሞቹስ ያዕቆብ፣ ዮሴፍ፣ ስምዖንና ይሁዳ አይደሉም?+ ማርቆስ 3:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 በዚህ ጊዜ እናቱና ወንድሞቹ+ መጡ፤ ውጭ ቆመውም ሰው ልከው አስጠሩት።+ ሉቃስ 8:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ከዚህ በኋላ እናቱና ወንድሞቹ+ እሱ ወዳለበት መጡ፤ ሆኖም ከሕዝቡ ብዛት የተነሳ ወደ እሱ ሊቀርቡ አልቻሉም።+ የሐዋርያት ሥራ 1:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 እነዚህ ሁሉ ከአንዳንድ ሴቶችና+ ከኢየሱስ እናት ከማርያም እንዲሁም ከወንድሞቹ+ ጋር በአንድ ልብ ተግተው ይጸልዩ ነበር።