ኢሳይያስ 50:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ለሚገርፉኝ ጀርባዬን፣ጢም ለሚነጩም ጉንጮቼን ሰጠሁ። ፊቴን፣ ከሚያዋርዱ ነገሮችና ከትፋት አልሰወርኩም።+ ማቴዎስ 20:18, 19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 “እነሆ፣ ወደ ኢየሩሳሌም እየወጣን ነው፤ የሰው ልጅ ለካህናት አለቆችና ለጸሐፍት አልፎ ይሰጣል። እነሱም ሞት ይፈርዱበታል፤+ 19 እንዲሁም እንዲያፌዙበት፣ እንዲገርፉትና በእንጨት ላይ እንዲሰቅሉት ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤+ እሱም በሦስተኛው ቀን ይነሳል።”+ ማቴዎስ 27:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 ከዚያም በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን ካስገረፈው በኋላ+ በእንጨት ላይ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠው።+ ማርቆስ 15:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 በዚህ ጊዜ ጲላጦስ ሕዝቡን ለማስደሰት ስለፈለገ በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስንም ካስገረፈው+ በኋላ በእንጨት ላይ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠው።+
18 “እነሆ፣ ወደ ኢየሩሳሌም እየወጣን ነው፤ የሰው ልጅ ለካህናት አለቆችና ለጸሐፍት አልፎ ይሰጣል። እነሱም ሞት ይፈርዱበታል፤+ 19 እንዲሁም እንዲያፌዙበት፣ እንዲገርፉትና በእንጨት ላይ እንዲሰቅሉት ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤+ እሱም በሦስተኛው ቀን ይነሳል።”+