63 ኢየሱስ ግን ዝም አለ።+ ሊቀ ካህናቱም “አንተ የአምላክ ልጅ ክርስቶስ መሆን አለመሆንህን እንድትነግረን በሕያው አምላክ አስምልሃለሁ!” አለው።+ 64 ኢየሱስም “አንተው ራስህ ተናገርከው። ነገር ግን እላችኋለሁ፦ ከዚህ በኋላ የሰው ልጅ+ በኃያሉ ቀኝ ተቀምጦ+ በሰማይ ደመና ሲመጣ ታያላችሁ”+ አለው። 65 በዚህ ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ እንዲህ አለ፦ “አምላክን ተሳድቧል! ከዚህ በላይ ምን ምሥክሮች ያስፈልጉናል? ስድቡን እንደሆነ እናንተም ሰምታችኋል።