-
ዘፍጥረት 41:40-46አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
40 አንተው ራስህ በቤቴ ላይ ትሾማለህ፤ ሕዝቤም ሁሉ ያላንዳች ማንገራገር ይታዘዝልሃል።+ እኔ ከአንተ የምበልጠው ንጉሥ በመሆኔ* ብቻ ይሆናል።” 41 በመቀጠልም ፈርዖን ዮሴፍን “ይኸው በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ሾሜሃለሁ” አለው።+ 42 ከዚያም ፈርዖን የማኅተም ቀለበቱን ከእጁ ላይ አውልቆ በዮሴፍ እጅ ላይ አደረገለት፤ ከጥሩ የተልባ እግር የተሠራ ልብስም አለበሰው፤ በአንገቱም ላይ የወርቅ ሐብል አጠለቀለት። 43 ከዚህም በላይ ከእሱ ቀጥሎ ባለው የክብር ሠረገላው ላይ አስቀመጠው፤ ሰዎችም ከፊት ከፊቱ እየሄዱ “አቭሬክ!”* እያሉ ይጮኹ ነበር። በዚህ መንገድ በመላው የግብፅ ምድር ላይ ሾመው።
44 በተጨማሪም ፈርዖን ዮሴፍን “እኔ ፈርዖን ነኝ፤ ሆኖም ያለአንተ ፈቃድ ማንም ሰው በመላው የግብፅ ምድር ላይ ምንም ነገር ማድረግ* አይችልም” አለው።+ 45 ከዚያም ፈርዖን ለዮሴፍ ጸፍናትፓነህ የሚል ስም አወጣለት፤ የኦን* ካህን የሆነውን የጶጥፌራን ልጅ አስናትንም+ አጋባው። ዮሴፍም መላውን የግብፅ ምድር መቃኘት* ጀመረ።+ 46 ዮሴፍ በግብፁ ንጉሥ በፈርዖን ፊት በቆመ* ጊዜ ዕድሜው 30 ዓመት+ ነበር።
ከዚያም ዮሴፍ ከፈርዖን ፊት ወጣ፤ መላውን የግብፅ ምድርም ተዘዋውሮ ተመለከተ።
-