-
ዘፀአት 2:11-15አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 ሙሴ በጎለመሰ ጊዜ* ወንድሞቹ የተጫነባቸውን ሸክም+ ለማየት ወደ እነሱ ወጣ፤ ከዚያም ከወንድሞቹ አንዱ የሆነውን ዕብራዊ አንድ ግብፃዊ ሲደበድበው አየ። 12 በመሆኑም ወዲያና ወዲህ ተመልክቶ ማንም አለመኖሩን ካረጋገጠ በኋላ ግብፃዊውን ገድሎ አሸዋ ውስጥ ደበቀው።+
13 ሆኖም በማግስቱ ሲወጣ ሁለት ዕብራውያን እርስ በርሳቸው ሲጣሉ ተመለከተ። እሱም ጥፋተኛውን “የገዛ ወገንህን የምትመታው ለምንድን ነው?” አለው።+ 14 በዚህ ጊዜ “አንተን በእኛ ላይ አለቃና ፈራጅ ማን አደረገህ? ግብፃዊውን እንደገደልከው እኔንም ልትገድለኝ ታስባለህ?” አለው።+ ሙሴም “ይህ ነገር ታውቋል ማለት ነው!” ብሎ በማሰብ ፈራ።
15 ከዚያም ፈርዖን ይህን ነገር ሰማ፤ ሙሴንም ሊገድለው ሞከረ፤ ይሁን እንጂ ሙሴ ከፈርዖን ሸሽቶ በምድያም+ ምድር ለመኖር ሄደ፤ እዚያም በአንድ የውኃ ጉድጓድ አጠገብ ተቀመጠ።
-