-
ዘፀአት 3:2-10አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 ከዚያም የይሖዋ መልአክ በቁጥቋጦ መሃል በሚነድ የእሳት ነበልባል ውስጥ ተገለጠለት።+ እሱም ትኩር ብሎ ሲመለከት ቁጥቋጦው በእሳት ቢያያዝም አለመቃጠሉን አስተዋለ። 3 ስለዚህ ሙሴ “ይህ እንግዳ ነገር ምን እንደሆነ ለማወቅና ቁጥቋጦው የማይቃጠለው ለምን እንደሆነ ለማየት እስቲ ቀረብ ልበል” አለ። 4 ይሖዋም ሙሴ ሁኔታውን ለማየት ቀረብ ማለቱን ሲመለከት ከቁጥቋጦው መሃል “ሙሴ! ሙሴ!” ሲል ጠራው፤ እሱም “አቤት” አለ። 5 ከዚያም አምላክ “ከዚህ በላይ እንዳትቀርብ። የቆምክበት ስፍራ ቅዱስ መሬት ስለሆነ ጫማህን አውልቅ” አለው።
6 እሱም በመቀጠል “እኔ የአባትህ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣+ የይስሐቅ አምላክና+ የያዕቆብ አምላክ+ ነኝ” አለው። በዚህ ጊዜ ሙሴ እውነተኛውን አምላክ ለማየት ስለፈራ ፊቱን ከለለ። 7 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “በግብፅ የሚኖረውን የሕዝቤን መከራ በእርግጥ አይቻለሁ፤ አስገድደው በሚያሠሯቸው ሰዎች የተነሳ የሚያሰሙትን ጩኸት ሰምቻለሁ፤ እየደረሰባቸው ያለውንም ሥቃይ በሚገባ አውቃለሁ።+ 8 እኔም ከግብፃውያን እጅ ልታደጋቸው+ እንዲሁም ከዚያ ምድር አውጥቼ ወደ ከነአናውያን፣ ወደ ሂታውያን፣ ወደ አሞራውያን፣ ወደ ፈሪዛውያን፣ ወደ ሂዋውያንና ወደ ኢያቡሳውያን ግዛት ይኸውም ወተትና ማር ወደምታፈሰው መልካምና ሰፊ ምድር+ ላስገባቸው እወርዳለሁ።+ 9 እነሆ የእስራኤል ሕዝብ የሚያሰማው ጩኸት ወደ እኔ ደርሷል፤ ግብፃውያኑ እነሱን በመጨቆን እያደረሱባቸው ያለውን በደል ተመልክቻለሁ።+ 10 ስለዚህ አሁን ና፤ ወደ ፈርዖን እልክሃለሁ፤ አንተም ሕዝቤን እስራኤልን ከግብፅ ታወጣለህ።”+
-