የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የሐዋርያት ሥራ 22:6-11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 6 “ሆኖም በጉዞ ላይ ሳለሁ ወደ ደማስቆ ስቃረብ፣ እኩለ ቀን ገደማ ላይ ድንገት ከሰማይ የመጣ ኃይለኛ ብርሃን በዙሪያዬ አንጸባረቀ፤+ 7 እኔም መሬት ላይ ወደቅኩ፤ ከዚያም ‘ሳኦል፣ ሳኦል ለምን ታሳድደኛለህ?’ የሚል ድምፅ ሰማሁ። 8 እኔም መልሼ ‘ጌታዬ፣ አንተ ማን ነህ?’ አልኩት። እሱም ‘እኔ አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ’ አለኝ። 9 ከእኔ ጋር የነበሩት ሰዎች ብርሃኑን አይተዋል፤ ሆኖም እሱ ሲያነጋግረኝ ድምፁን አልሰሙም።* 10 በዚህ ጊዜ ‘ጌታ ሆይ፣ ምን ባደርግ ይሻላል?’ አልኩት። ጌታም ‘ተነስተህ ወደ ደማስቆ ሂድ፤ እዚያም ልታደርገው የሚገባህ ነገር ሁሉ ይነገርሃል’ አለኝ።+ 11 ይሁንና ከብርሃኑ ድምቀት የተነሳ ዓይኔ ማየት ስለተሳነው አብረውኝ የነበሩት ሰዎች እጄን ይዘው እየመሩ ደማስቆ አደረሱኝ።

  • የሐዋርያት ሥራ 26:13-18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ንጉሥ ሆይ፣ እኩለ ቀን ሲሆን በመንገድ ላይ ከፀሐይ ብርሃን የበለጠ ድምቀት ያለው ከሰማይ የመጣ ብርሃን በእኔና አብረውኝ በሚጓዙት ሰዎች ዙሪያ ሲያበራ አየሁ።+ 14 ሁላችንም መሬት ላይ በወደቅን ጊዜ አንድ ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ‘ሳኦል፣ ሳኦል ለምን ታሳድደኛለህ? መውጊያውን* መቃወምህን ከቀጠልክ ለአንተው የባሰ ይሆንብሃል’ ሲለኝ ሰማሁ። 15 እኔም ‘ጌታዬ፣ አንተ ማን ነህ?’ አልኩ። ጌታም እንዲህ አለኝ፦ ‘እኔ አንተ የምታሳድደኝ ኢየሱስ ነኝ። 16 ይሁንና አሁን ተነስተህ በእግርህ ቁም። የተገለጥኩልህ እኔን በተመለከተ ስላየኸው ነገርና ወደፊት ስለማሳይህ ነገር አገልጋይና ምሥክር እንድትሆን አንተን ለመምረጥ ነው።+ 17 ወደ እነሱ ከምልክህ ከዚህ ሕዝብና ከአሕዛብ እታደግሃለሁ፤+ 18 የምልክህም የኃጢአት ይቅርታ ያገኙና+ በእኔ ላይ ባላቸው እምነት አማካኝነት በተቀደሱት መካከል ርስት ይቀበሉ ዘንድ ዓይናቸውን እንድትገልጥ+ እንዲሁም ከጨለማ+ ወደ ብርሃን፣+ ከሰይጣን ሥልጣንም+ ወደ አምላክ እንድትመልሳቸው ነው።’

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ