9 ዛሬ በእኛ ላይ ምርመራ እየተካሄደ ያለው ለአንድ ሽባ ሰው በተደረገ መልካም ሥራ+ የተነሳ ከሆነና ይህን ሰው ያዳነው ማን እንደሆነ ማወቅ የምትፈልጉ ከሆነ፣ 10 ይህ ሰው ጤናማ ሆኖ እዚህ ፊታችሁ የቆመው፣ እናንተ በእንጨት ላይ በሰቀላችሁት+ ሆኖም አምላክ ከሞት ባስነሳው+ በናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣+ ይኸውም በኢየሱስ አማካኝነት እንደሆነ እናንተም ሆናችሁ መላው የእስራኤል ሕዝብ ይወቅ።