የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የሐዋርያት ሥራ 11:5-10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 5 “በኢዮጴ ከተማ እየጸለይኩ ሳለ ሰመመን ውስጥ ሆኜ ራእይ አየሁ፤ አንድ ትልቅ ጨርቅ የሚመስል ነገር በአራቱም ጫፍ ተይዞ ከሰማይ ወረደና ወደ እኔ መጣ።+ 6 ይህን ነገር ትኩር ብዬ ስመለከት አራት እግር ያላቸው የምድር እንስሳት፣ የዱር አራዊት፣ በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትና የሰማይ ወፎች አየሁ። 7 በተጨማሪም አንድ ድምፅ ‘ጴጥሮስ፣ ተነሳና አርደህ ብላ!’ ሲለኝ ሰማሁ። 8 እኔ ግን ‘ጌታ ሆይ፣ በጭራሽ፤ ምክንያቱም ንጹሕ ያልሆነ ወይም የረከሰ ነገር ወደ አፌ ገብቶ አያውቅም’ አልኩ። 9 ለሁለተኛ ጊዜ ከሰማይ የመጣው ድምፅ ‘አምላክ ንጹሕ ያደረገውን ነገር ርኩስ ነው ማለትህን ተው’ ሲል መለሰልኝ። 10 ይህም ለሦስተኛ ጊዜ ተደገመ፤ ከዚያም ሁሉም ነገር እንደገና ወደ ሰማይ ተወሰደ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ