-
ዘሌዋውያን 11:4አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 “‘ሆኖም የሚያመሰኩትን ወይም ሰኮናቸው የተሰነጠቀውን እነዚህን እንስሳት መብላት የለባችሁም፦ ግመል የሚያመሰኳ ቢሆንም ሰኮናው የተሰነጠቀ አይደለም። ለእናንተ ርኩስ ነው።+
-
-
ዘሌዋውያን 11:13-20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
13 “‘ልትጸየፏቸው የሚገቡ በራሪ ፍጥረታት እነዚህ ናቸው፤ አስጸያፊ በመሆናቸው መበላት የለባቸውም፦ ንስር፣+ ዓሣ በል ጭላት፣ ጥቁር ጥምብ አንሳ፣+ 14 ቀይ ጭልፊት፣ ማንኛውም ዓይነት ጥቁር ጭልፊት፣ 15 ማንኛውም ዓይነት ቁራ፣ 16 ሰጎን፣ ጉጉት፣ ዓሣ አዳኝ፣ ማንኛውም ዓይነት ሲላ፣ 17 ትንሿ ጉጉት፣ ለማሚት፣ ባለ ረጅም ጆሮ ጉጉት፣ 18 ዝይ፣ ሻላ፣ ጥምብ አንሳ፣ 19 ራዛ፣ ማንኛውም ዓይነት ሽመላ፣ ጅንጅላቴና የሌሊት ወፍ። 20 በአራቱም እግሩ የሚሄድ ክንፍ ያለው የሚርመሰመስ ፍጡር* ሁሉ ለእናንተ አስጸያፊ ነው።
-
-
ዘዳግም 14:3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 “ማንኛውንም አስጸያፊ ነገር አትብላ።+
-