የሐዋርያት ሥራ 13:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 እነዚህ ይሖዋን* እያገለገሉና* እየጾሙ ሳሉ መንፈስ ቅዱስ “በርናባስንና ሳኦልን አንድ ሥራ እንዲሠሩ ስለመረጥኳቸው ለዩልኝ”+ አለ። የሐዋርያት ሥራ 15:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 ከሚከተሉት አስፈላጊ ነገሮች በስተቀር፣ ሌላ ተጨማሪ ሸክም እንዳንጭንባችሁ መንፈስ ቅዱስና+ እኛ ወስነናል፦ የሐዋርያት ሥራ 16:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ከዚህም ሌላ መንፈስ ቅዱስ ቃሉን በእስያ አውራጃ እንዳይናገሩ ስለከለከላቸው በፍርግያና በገላትያ አድርገው አለፉ።+ የሐዋርያት ሥራ 20:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 እርግጥ ነው፣ እስራትና መከራ እንደሚጠብቀኝ መንፈስ ቅዱስ በደረስኩበት ከተማ ሁሉ በተደጋጋሚ ያሳስበኛል።+