-
የሐዋርያት ሥራ 14:12-15አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 በርናባስን ዙስ፣ ጳውሎስን ደግሞ ዋና ተናጋሪ ስለነበር ሄርሜስ ብለው ይጠሯቸው ጀመር። 13 በከተማዋ መግቢያ ላይ ይገኝ የነበረው የዙስ ቤተ መቅደስ ካህን፣ ኮርማዎችና የአበባ ጉንጉን ወደ ከተማዋ መግቢያ በማምጣት ከሕዝቡ ጋር ሆኖ መሥዋዕት ሊሠዋላቸው ፈለገ።
14 ይሁን እንጂ ሐዋርያቱ በርናባስና ጳውሎስ ይህን ሲሰሙ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ሮጠውም ሕዝቡ መሃል በመግባት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እንዲህ አሉ፦ 15 “እናንተ ሰዎች፣ እንዲህ የምታደርጉት ለምንድን ነው? እኛም እንደ እናንተው ድክመት ያለብን ሰዎች ነን።+ ምሥራቹን እያወጅንላችሁ ያለነውም እነዚህን ከንቱ ነገሮች ትታችሁ ሰማይን፣ ምድርን፣ ባሕርንና በውስጣቸው ያሉትን ነገሮች ሁሉ የፈጠረውን ሕያው አምላክ እንድታመልኩ ነው።+
-