-
ዘዳግም 16:9-11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 “ሰባት ሳምንት ቁጠር። ሰባቱን ሳምንት መቁጠር መጀመር ያለብህ በማሳህ ላይ ያለውን እህል ለማጨድ ማጭድህን ካነሳህበት ጊዜ አንስቶ ነው።+ 10 ከዚያም አምላክህ ይሖዋ በባረከህ መጠን+ በምታቀርበው የፈቃደኝነት መባ አማካኝነት ለአምላክህ ለይሖዋ የሳምንታት በዓልን ታከብራለህ።+ 11 በአምላክህ በይሖዋ ፊት ደስ ይበልህ፤ አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ፣ ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህ፣ ሴት ባሪያህ እንዲሁም በከተሞችህ ውስጥ* የሚኖር ሌዋዊ፣ በመካከልህ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው፣ አባት የሌለው* ልጅና መበለቲቱ አምላክህ ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በመረጠው ስፍራ ደስ ይበላችሁ።+
-