-
ማቴዎስ 20:20-23አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 ከዚያም የዘብዴዎስ+ ሚስት ከልጆቿ ጋር ወደ እሱ ቀርባ እየሰገደች* አንድ ነገር እንዲያደርግላት ለመነችው።+ 21 እሱም “ምንድን ነው የፈለግሽው?” አላት። እሷም መልሳ “በመንግሥትህ እነዚህን ሁለቱን ልጆቼን፣ አንዱን በቀኝህ አንዱን ደግሞ በግራህ አስቀምጥልኝ” አለችው።+ 22 ኢየሱስም መልሶ “የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ በቅርቡ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡ ትችላላችሁ?” አላቸው።+ እነሱም “እንችላለን” አሉት። 23 እሱም “በእርግጥ የእኔን ጽዋ ትጠጣላችሁ፤+ በቀኜ ወይም በግራዬ መቀመጥ ግን አባቴ ላዘጋጀላቸው የሚሰጥ እንጂ በእኔ ፈቃድ የሚሆን አይደለም” አላቸው።+
-
-
ሉቃስ 11:49አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
49 ስለዚህ የአምላክ ጥበብ እንዲህ አለች፦ ‘ነቢያትንና ሐዋርያትን ወደ እነሱ እልካለሁ፤ እነሱም አንዳንዶቹን ይገድላሉ በአንዳንዶቹም ላይ ስደት ያደርሳሉ፤
-