13 በዚህ ጊዜ ሳሙኤል ሳኦልን እንዲህ አለው፦ “የፈጸምከው የሞኝነት ድርጊት ነው። አምላክህ ይሖዋ የሰጠህን ትእዛዝ አልጠበቅክም።+ ጠብቀህ ቢሆን ኖሮ ይሖዋ መንግሥትህን በእስራኤል ላይ ለዘላለም ባጸናልህ ነበር። 14 አሁን ግን መንግሥትህ አይዘልቅም።+ ይሖዋ እንደ ልቡ የሚሆንለት ሰው ያገኛል፤+ ይሖዋም በሕዝቡ ላይ መሪ አድርጎ ይሾመዋል፤+ ምክንያቱም አንተ የይሖዋን ትእዛዝ አልጠበቅክም።”+