1 ሳሙኤል 16:12, 13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 በመሆኑም ልኮ አስመጣው። እሱም የቀይ ዳማ፣ ዓይኑ የሚያምርና መልከ መልካም ነበር።+ ከዚያም ይሖዋ “ተነስ፣ ቀባው፤ የመረጥኩት እሱን ነው!” አለው።+ 13 ስለዚህ ሳሙኤል የዘይቱን ቀንድ+ ወስዶ በወንድሞቹ ፊት ቀባው። ከዚያም ቀን አንስቶ የይሖዋ መንፈስ ለዳዊት ኃይል ሰጠው።+ በኋላም ሳሙኤል ተነስቶ ወደ ራማ+ ሄደ። መዝሙር 89:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 አገልጋዬን ዳዊትን አገኘሁት፤+በተቀደሰ ዘይቴም ቀባሁት።+
12 በመሆኑም ልኮ አስመጣው። እሱም የቀይ ዳማ፣ ዓይኑ የሚያምርና መልከ መልካም ነበር።+ ከዚያም ይሖዋ “ተነስ፣ ቀባው፤ የመረጥኩት እሱን ነው!” አለው።+ 13 ስለዚህ ሳሙኤል የዘይቱን ቀንድ+ ወስዶ በወንድሞቹ ፊት ቀባው። ከዚያም ቀን አንስቶ የይሖዋ መንፈስ ለዳዊት ኃይል ሰጠው።+ በኋላም ሳሙኤል ተነስቶ ወደ ራማ+ ሄደ።