-
ማቴዎስ 17:18አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 ከዚያም ኢየሱስ ጋኔኑን ገሠጸው፤ ጋኔኑም ከልጁ ወጣ፤ ልጁም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ተፈወሰ።+
-
-
ማርቆስ 1:25, 26አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
25 ሆኖም ኢየሱስ “ዝም በል፤ ከእሱም ውጣ!” ብሎ ገሠጸው። 26 ርኩሱም መንፈስ ሰውየውን ጥሎ ካንፈራገጠው በኋላ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ከእሱ ወጣ።
-
-
ሉቃስ 10:17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 ከዚያም 70ዎቹ ደስ እያላቸው ተመልሰው “ጌታ ሆይ፣ አጋንንት እንኳ በስምህ ተገዙልን” አሉት።+
-