መዝሙር 22:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 የሚያዩኝ ሁሉ ያላግጡብኛል፤+በንቀትና በፌዝ ጭንቅላታቸውን እየነቀነቁ እንዲህ ይሉኛል፦+ መዝሙር 34:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 አጥንቶቹን ሁሉ ይጠብቃል፤አንዳቸውም ቢሆኑ አልተሰበሩም።+ መዝሙር 69:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ይልቁንም መርዝ* እንድበላ ሰጡኝ፤+በጠማኝ ጊዜም ኮምጣጤ እንድጠጣ ሰጡኝ።+ መዝሙር 118:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ግንበኞች የናቁት ድንጋይየማዕዘን ራስ ድንጋይ* ሆነ።+ ኢሳይያስ 50:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ለሚገርፉኝ ጀርባዬን፣ጢም ለሚነጩም ጉንጮቼን ሰጠሁ። ፊቴን፣ ከሚያዋርዱ ነገሮችና ከትፋት አልሰወርኩም።+ ኢሳይያስ 53:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ሰዎች የናቁትና ያገለሉት፣+ሥቃይን ያየ፣* ሕመምንም የሚያውቅ ሰው ነበር። ፊቱ የተሰወረብን ያህል ነበር።* ሰዎች ናቁት፤ እኛም ከቁብ አልቆጠርነውም።+ ኢሳይያስ 53:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 እሱ ግን ስለ መተላለፋችን+ ተወጋ፤+ስለ በደላችን ደቀቀ።+ በእሱ ላይ የደረሰው ቅጣት ለእኛ ሰላም አስገኘልን፤+በእሱም ቁስል የተነሳ እኛ ተፈወስን።+