ሮም 8:34 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 እነሱን የሚኮንን ማን ነው? ምክንያቱም የሞተው ብሎም ከሞት የተነሳውና በአምላክ ቀኝ የተቀመጠው+ እንዲሁም ስለ እኛ የሚማልደው+ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ፊልጵስዩስ 2:9-11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 በዚህም ምክንያት አምላክ የላቀ ቦታ በመስጠት ከፍ ከፍ አደረገው፤+ እንዲሁም ከሌላ ከማንኛውም ስም በላይ የሆነ ስም በደግነት ሰጠው፤+ 10 ይህም በሰማይና በምድር እንዲሁም ከምድር በታች ያሉ ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ ነው፤+ 11 ምላስም ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ በመመሥከር+ አባት ለሆነው አምላክ ክብር ያመጣ ዘንድ ነው። 1 ጴጥሮስ 3:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ኢየሱስ ወደ ሰማይ የሄደ ሲሆን አሁን በአምላክ ቀኝ ይገኛል፤+ እንዲሁም መላእክት፣ ሥልጣናትና ኃይላት እንዲገዙለት ተደርጓል።+
9 በዚህም ምክንያት አምላክ የላቀ ቦታ በመስጠት ከፍ ከፍ አደረገው፤+ እንዲሁም ከሌላ ከማንኛውም ስም በላይ የሆነ ስም በደግነት ሰጠው፤+ 10 ይህም በሰማይና በምድር እንዲሁም ከምድር በታች ያሉ ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ ነው፤+ 11 ምላስም ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ በመመሥከር+ አባት ለሆነው አምላክ ክብር ያመጣ ዘንድ ነው።