ሉቃስ 24:46, 47 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 46 እንዲህም አላቸው፦ “እንደሚከተለው ተብሎ ተጽፏል፤ ክርስቶስ መከራ ይቀበላል፤ በሦስተኛውም ቀን ከሞት ይነሳል፤+ 47 በስሙም የኃጢአት ይቅርታ የሚያስገኝ+ ንስሐ ከኢየሩሳሌም አንስቶ+ ለብሔራት ሁሉ ይሰበካል።+ የሐዋርያት ሥራ 17:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 እርግጥ አምላክ ሰዎች ባለማወቅ የኖሩበትን ጊዜ+ ችላ ብሎ አልፎታል፤ አሁን ግን በየቦታው ያሉ ሰዎች ሁሉ ንስሐ እንዲገቡ እያሳሰበ ነው። የሐዋርያት ሥራ 26:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ከዚህ ይልቅ በመጀመሪያ በደማስቆ+ ላሉ ቀጥሎም በኢየሩሳሌምና+ በመላው የይሁዳ አገር ሁሉ ለሚገኙ ከዚያም ለአሕዛብ ንስሐ እንዲገቡና ለንስሐ የሚገባ ሥራ+ በመሥራት ወደ አምላክ እንዲመለሱ የሚያሳስበውን መልእክት ማዳረሴን ቀጠልኩ።
46 እንዲህም አላቸው፦ “እንደሚከተለው ተብሎ ተጽፏል፤ ክርስቶስ መከራ ይቀበላል፤ በሦስተኛውም ቀን ከሞት ይነሳል፤+ 47 በስሙም የኃጢአት ይቅርታ የሚያስገኝ+ ንስሐ ከኢየሩሳሌም አንስቶ+ ለብሔራት ሁሉ ይሰበካል።+
20 ከዚህ ይልቅ በመጀመሪያ በደማስቆ+ ላሉ ቀጥሎም በኢየሩሳሌምና+ በመላው የይሁዳ አገር ሁሉ ለሚገኙ ከዚያም ለአሕዛብ ንስሐ እንዲገቡና ለንስሐ የሚገባ ሥራ+ በመሥራት ወደ አምላክ እንዲመለሱ የሚያሳስበውን መልእክት ማዳረሴን ቀጠልኩ።