20 እሱም እንዲህ አለ፦ “አይሁዳውያን ስለ ጳውሎስ ጉዳይ በዝርዝር ማወቅ የፈለጉ በማስመሰል ነገ ወደ ሳንሄድሪን ሸንጎ እንድታመጣው ሊጠይቁህ ተስማምተዋል።+ 21 አንተ ግን በዚህ እንዳትታለል፤ ምክንያቱም ከመካከላቸው ከ40 በላይ የሚሆኑ ሰዎች አድብተው በእሱ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እየጠበቁ ነው፤ ደግሞም እሱን እስኪገድሉ ድረስ እህልም ሆነ ውኃ ላለመቅመስ ተማምለዋል፤+ አሁንም ተዘጋጅተው የአንተን ፈቃድ እየተጠባበቁ ነው።”