መዝሙር 22:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 የሚያዩኝ ሁሉ ያላግጡብኛል፤+በንቀትና በፌዝ ጭንቅላታቸውን እየነቀነቁ እንዲህ ይሉኛል፦+ መዝሙር 35:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ያላንዳች ምክንያት ጠላቶቼ የሆኑ እኔን አይተው እንዲፈነድቁ፣ያለምክንያት የሚጠሉኝ+ በተንኮል እንዲጠቃቀሱብኝ አትፍቀድ።+ ኢሳይያስ 50:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ለሚገርፉኝ ጀርባዬን፣ጢም ለሚነጩም ጉንጮቼን ሰጠሁ። ፊቴን፣ ከሚያዋርዱ ነገሮችና ከትፋት አልሰወርኩም።+ ኢሳይያስ 53:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 እሱ ግን ስለ መተላለፋችን+ ተወጋ፤+ስለ በደላችን ደቀቀ።+ በእሱ ላይ የደረሰው ቅጣት ለእኛ ሰላም አስገኘልን፤+በእሱም ቁስል የተነሳ እኛ ተፈወስን።+