የሐዋርያት ሥራ 23:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ጳውሎስ ግማሾቹ ሰዱቃውያን ግማሾቹ ደግሞ ፈሪሳውያን መሆናቸውን ስላወቀ በሳንሄድሪን ሸንጎ ውስጥ ድምፁን ከፍ አድርጎ “ወንድሞች፣ እኔ ከፈሪሳውያን የተወለድኩ ፈሪሳዊ ነኝ።+ ለፍርድ የቀረብኩት በሙታን ትንሣኤ ተስፋ በማመኔ ነው” ሲል ተናገረ። የሐዋርያት ሥራ 26:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 አሁን ግን እዚህ ለፍርድ የቀረብኩት አምላክ ለአባቶቻችን የገባውን ቃል ተስፋ በማድረጌ ነው፤+ ኤፌሶን 6:19, 20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 የምሥራቹን ቅዱስ ሚስጥር በድፍረት ለሌሎች ማሳወቅ እንድችል አፌን በምከፍትበት ጊዜ የምናገረው ቃል እንዲሰጠኝ ለእኔም ጸልዩልኝ፤+ 20 በሰንሰለት የታሰረ አምባሳደር ሆኜ እያገለገልኩ+ ያለሁት ለዚሁ ምሥራች ነው፤ ስለ ምሥራቹ የሚገባኝን ያህል በድፍረት መናገር እንድችል ጸልዩልኝ። 2 ጢሞቴዎስ 1:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ጌታ ለኦኔሲፎሮስ+ ቤተሰብ ምሕረትን ይስጥ፤ እሱ ብዙ ጊዜ መንፈሴን አድሶልኛልና፤ በታሰርኩበት ሰንሰለትም አላፈረም።
6 ጳውሎስ ግማሾቹ ሰዱቃውያን ግማሾቹ ደግሞ ፈሪሳውያን መሆናቸውን ስላወቀ በሳንሄድሪን ሸንጎ ውስጥ ድምፁን ከፍ አድርጎ “ወንድሞች፣ እኔ ከፈሪሳውያን የተወለድኩ ፈሪሳዊ ነኝ።+ ለፍርድ የቀረብኩት በሙታን ትንሣኤ ተስፋ በማመኔ ነው” ሲል ተናገረ።
19 የምሥራቹን ቅዱስ ሚስጥር በድፍረት ለሌሎች ማሳወቅ እንድችል አፌን በምከፍትበት ጊዜ የምናገረው ቃል እንዲሰጠኝ ለእኔም ጸልዩልኝ፤+ 20 በሰንሰለት የታሰረ አምባሳደር ሆኜ እያገለገልኩ+ ያለሁት ለዚሁ ምሥራች ነው፤ ስለ ምሥራቹ የሚገባኝን ያህል በድፍረት መናገር እንድችል ጸልዩልኝ።