መዝሙር 67:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ይህም መንገድህ በምድር ሁሉ ላይ፣+የማዳን ሥራህም በብሔራት ሁሉ መካከል እንዲታወቅ ነው።+ መዝሙር 98:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ለእስራኤል ቤት ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት ለማሳየት የገባውን ቃል አስታውሷል።+ የምድር ዳርቻዎች ሁሉ የአምላካችንን ማዳን* አይተዋል።+ ኢሳይያስ 11:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 በዚያን ቀን የእሴይ ሥር+ ለሕዝቦች ምልክት* ሆኖ ይቆማል።+ ብሔራት ከእሱ መመሪያ ይሻሉ፤*+ማረፊያ ስፍራውም እጅግ የከበረ ይሆናል።