-
ፊልጵስዩስ 1:18-20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 ታዲያ ይህ ምን አስከተለ? በማስመሰልም ሆነ በእውነት፣ በሁሉም መንገድ ክርስቶስ እንዲሰበክ አስችሏል፤ በዚህ ደግሞ ደስተኛ ነኝ። ወደፊትም ቢሆን መደሰቴን እቀጥላለሁ፤ 19 ይህ በእናንተ ምልጃ+ እንዲሁም የኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ በሚሰጠኝ ድጋፍ+ መዳን እንደሚያስገኝልኝ አውቃለሁና። 20 ይህም በጉጉት ከምጠባበቀው ነገርና ከተስፋዬ ጋር በሚስማማ ሁኔታ በማንኛውም መንገድ እንዳላፍር ነው፤ ከዚህ ይልቅ በነፃነት በመናገር በሕይወትም ሆነ በሞት እንደ ወትሮው ሁሉ አሁንም ክርስቶስን በሰውነቴ አማካኝነት ከፍ ከፍ አደርገው ዘንድ ነው።+
-