7 ከብዙ ክርክር በኋላ ጴጥሮስ ተነስቶ እንዲህ አላቸው፦ “ወንድሞች፣ አሕዛብ የምሥራቹን ቃል ከእኔ አፍ ሰምተው እንዲያምኑ አምላክ ገና ከመጀመሪያው ከእናንተ መካከል እኔን እንደመረጠኝ በሚገባ ታውቃላችሁ።+ 8 ልብን የሚያውቀው አምላክ+ ለእኛ እንዳደረገው ሁሉ ለእነሱም መንፈስ ቅዱስን በመስጠት መሠከረላቸው።+ 9 ደግሞም በእኛና በእነሱ መካከል ምንም ልዩነት አላደረገም፤+ ከዚህ ይልቅ በእምነታቸው የተነሳ ልባቸውን አነጻ።+