1 ቆሮንቶስ 9:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ደካሞችን እማርክ ዘንድ ለደካሞች ደካማ ሆንኩ።+ በተቻለ መጠን የተወሰኑ ሰዎችን አድን ዘንድ ለሁሉም ዓይነት ሰዎች ሁሉንም ነገር ሆንኩ። ፊልጵስዩስ 2:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ስለ ራሳችሁ ፍላጎት ብቻ ከማሰብ ይልቅ+ እያንዳንዳችሁ ለሌሎች ሰዎች ፍላጎትም ትኩረት ስጡ።+