ዘዳግም 30:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ቃሉ ትፈጽመው ዘንድ+ ለአንተ በጣም ቅርብ ነውና፤ ደግሞም በአፍህና በልብህ ውስጥ ነው።+ ሕዝቅኤል 20:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 “‘“ከዚያም ደንቦቼን ሰጠኋቸው፤ ድንጋጌዎቼንም አሳወቅኳቸው፤+ ይህን ያደረግኩት እነሱን የሚከተል ሰው በእነሱ አማካኝነት በሕይወት እንዲኖር ነው።+ ያዕቆብ 1:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ሆኖም ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ+ እንጂ የውሸት ምክንያት እያቀረባችሁ ራሳችሁን በማታለል ሰሚዎች ብቻ አትሁኑ።