ሮም 12:4, 5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 በአንድ አካል ላይ ብዙ የአካል ክፍሎች አሉን፤+ ደግሞም ሁሉም የአካል ክፍሎች አንድ ዓይነት ተግባር አያከናውኑም፤ 5 ልክ እንደዚሁ እኛም ብዙ ብንሆንም እንኳ ከክርስቶስ ጋር ባለን አንድነት አንድ አካል ነን፤ ደግሞም አንዳችን የሌላው የአካል ክፍል ነን።+ 1 ቆሮንቶስ 12:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ሆኖም አምላክ እያንዳንዱን የአካል ክፍል እሱ በፈለገው ቦታ መድቦታል። 1 ቆሮንቶስ 12:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 እንግዲህ እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ፤+ እያንዳንዳችሁም በግለሰብ ደረጃ የአካሉ ክፍል ናችሁ።+ ኤፌሶን 4:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ከዚህ ይልቅ እውነትን በመናገር በሁሉም ነገር ወደ እሱ ይኸውም የአካሉ ራስ ወደሆነው ወደ ክርስቶስ+ በፍቅር እንደግ። ኤፌሶን 5:29, 30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 የገዛ አካሉን* የሚጠላ ማንም ሰው የለምና፤ ከዚህ ይልቅ ይመግበዋል እንዲሁም ይሳሳለታል፤ ክርስቶስም ለጉባኤው ያደረገው እንደዚሁ ነው፤ 30 ምክንያቱም እኛ የእሱ አካል ክፍሎች ነን።+
4 በአንድ አካል ላይ ብዙ የአካል ክፍሎች አሉን፤+ ደግሞም ሁሉም የአካል ክፍሎች አንድ ዓይነት ተግባር አያከናውኑም፤ 5 ልክ እንደዚሁ እኛም ብዙ ብንሆንም እንኳ ከክርስቶስ ጋር ባለን አንድነት አንድ አካል ነን፤ ደግሞም አንዳችን የሌላው የአካል ክፍል ነን።+
29 የገዛ አካሉን* የሚጠላ ማንም ሰው የለምና፤ ከዚህ ይልቅ ይመግበዋል እንዲሁም ይሳሳለታል፤ ክርስቶስም ለጉባኤው ያደረገው እንደዚሁ ነው፤ 30 ምክንያቱም እኛ የእሱ አካል ክፍሎች ነን።+