-
ዘሌዋውያን 6:14አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 “‘የእህል መባ ሕግ ደግሞ ይህ ነው፦+ እናንተ የአሮን ወንዶች ልጆች በመሠዊያው ፊት ለፊት በይሖዋ ፊት ታቀርቡታላችሁ።
-
-
ዘኁልቁ 18:30, 31አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
30 “እንዲህም በላቸው፦ ‘ከስጦታዎቹ ላይ ምርጥ የሆነውን በምታዋጡበት ጊዜ ይህ ለእናንተ ለሌዋውያኑ ከአውድማ እንደገባ ምርት እንዲሁም ከወይን መጭመቂያ ወይም ከዘይት መጭመቂያ እንደተገኘ ምርት ተደርጎ ይታሰብላችኋል። 31 ይህ በመገናኛ ድንኳኑ ለምታከናውኑት አገልግሎት የተሰጠ ደሞዛችሁ ስለሆነ እናንተም ሆናችሁ ቤተሰባችሁ በየትኛውም ቦታ ልትበሉት ትችላላችሁ።+
-
-
ዘዳግም 18:1አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 “ሌዋውያኑ ካህናት አልፎ ተርፎም መላው የሌዊ ነገድ ከእስራኤል ጋር ድርሻም ሆነ ውርሻ አይሰጣቸውም። የእሱ ድርሻ የሆኑትን ለይሖዋ በእሳት የሚቀርቡትን መባዎች ይበላሉ።+
-