8 እናንተን ለማገልገል ከሌሎች ጉባኤዎች ቁሳዊ እርዳታ በመቀበሌ እነሱን አራቁቻለሁ።+ 9 ከእናንተ ጋር ሳለሁ ተቸግሬ በነበረበት ጊዜ ከመቄዶንያ የመጡት ወንድሞች የጎደለኝን ነገር በሙሉ በሚገባ ስላሟሉልኝ ለማንም ሸክም አልሆንኩም።+ አዎ፣ እስካሁን ድረስ በእናንተ ላይ በምንም መንገድ ሸክም አልሆንኩም፤ ወደፊትም ሸክም አልሆንም።+ 10 የክርስቶስ እውነት በውስጤ እስካለ ድረስ በአካይያ ክልሎች ሁሉ በዚህ ነገር እንዳልኩራራ ምንም ነገር ሊያግደኝ አይችልም።+