ማቴዎስ 10:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 በስሜ የተነሳም ሰዎች ሁሉ ይጠሏችኋል፤+ እስከ መጨረሻው የጸና* ግን ይድናል።+ ፊልጵስዩስ 3:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 አምላክ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል የሚሰጠውን የሰማያዊውን ሕይወት+ ሽልማት አገኝ ዘንድ ግቡ ላይ ለመድረስ እየተጣጣርኩ ነው።+ 2 ጢሞቴዎስ 4:7, 8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፤+ ሩጫውን ጨርሻለሁ፤+ እምነትን ጠብቄአለሁ። 8 ከዚህ በኋላ የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶ ይጠብቀኛል፤+ ጻድቅ ፈራጅ+ የሆነው ጌታ በፍርድ ቀን ይህን እንደ ሽልማት አድርጎ ይሰጠኛል፤+ ይሁንና ለእኔ ብቻ ሳይሆን የእሱን መገለጥ ለሚናፍቁ ሁሉ ነው።
7 መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፤+ ሩጫውን ጨርሻለሁ፤+ እምነትን ጠብቄአለሁ። 8 ከዚህ በኋላ የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶ ይጠብቀኛል፤+ ጻድቅ ፈራጅ+ የሆነው ጌታ በፍርድ ቀን ይህን እንደ ሽልማት አድርጎ ይሰጠኛል፤+ ይሁንና ለእኔ ብቻ ሳይሆን የእሱን መገለጥ ለሚናፍቁ ሁሉ ነው።