ማቴዎስ 16:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ “የዮናስ ልጅ ስምዖን፣ ይህን የገለጠልህ ሥጋና ደም ሳይሆን* በሰማያት ያለው አባቴ ስለሆነ ደስ ይበልህ።+ ማርቆስ 4:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ለእናንተ የአምላክን መንግሥት ቅዱስ ሚስጥር+ የመረዳት ችሎታ ተሰጥቷችኋል፤ በውጭ ላሉት ግን የሚሰሙት ነገር ሁሉ እንዲሁ ምሳሌ ብቻ ሆኖ ይቀርባቸዋል፤+ ኤፌሶን 3:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ይህ ሚስጥር አሁን ለቅዱሳን ሐዋርያትና ነቢያት በመንፈስ እንደተገለጠው ባለፉት ትውልዶች ለነበሩ የሰው ልጆች አልተገለጠም ነበር።+ 2 ጢሞቴዎስ 1:9, 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 እሱ በእኛ ሥራ ሳይሆን በራሱ ዓላማና ጸጋ የተነሳ አዳነን፤+ እንዲሁም ቅዱስ በሆነ ጥሪ ጠራን።+ ይህን ጸጋ ከረጅም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት ሰጠን፤ 10 አሁን ግን ይህ ጸጋ አዳኛችን የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ በመገለጡ ግልጽ ሆኖ ታይቷል፤+ እሱ ሞትን አስወግዶ+ በምሥራቹ አማካኝነት+ ሕይወትንና አለመበስበስን+ በተመለከተ ብርሃን ፈንጥቋል፤+ 1 ጴጥሮስ 1:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 እነሱ ራሳቸውን እያገለገሉ እንዳልሆነ ተገልጦላቸው ነበር። ከዚህ ይልቅ ከሰማይ በተላከ መንፈስ ቅዱስ+ ምሥራቹን ባበሰሩላችሁ ሰዎች አማካኝነት ከተነገሯችሁ ነገሮች ጋር በተያያዘ እናንተን እያገለገሉ ነበር። መላእክትም እነዚህን ነገሮች ለማየት ይጓጓሉ።
11 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ለእናንተ የአምላክን መንግሥት ቅዱስ ሚስጥር+ የመረዳት ችሎታ ተሰጥቷችኋል፤ በውጭ ላሉት ግን የሚሰሙት ነገር ሁሉ እንዲሁ ምሳሌ ብቻ ሆኖ ይቀርባቸዋል፤+
9 እሱ በእኛ ሥራ ሳይሆን በራሱ ዓላማና ጸጋ የተነሳ አዳነን፤+ እንዲሁም ቅዱስ በሆነ ጥሪ ጠራን።+ ይህን ጸጋ ከረጅም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት ሰጠን፤ 10 አሁን ግን ይህ ጸጋ አዳኛችን የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ በመገለጡ ግልጽ ሆኖ ታይቷል፤+ እሱ ሞትን አስወግዶ+ በምሥራቹ አማካኝነት+ ሕይወትንና አለመበስበስን+ በተመለከተ ብርሃን ፈንጥቋል፤+
12 እነሱ ራሳቸውን እያገለገሉ እንዳልሆነ ተገልጦላቸው ነበር። ከዚህ ይልቅ ከሰማይ በተላከ መንፈስ ቅዱስ+ ምሥራቹን ባበሰሩላችሁ ሰዎች አማካኝነት ከተነገሯችሁ ነገሮች ጋር በተያያዘ እናንተን እያገለገሉ ነበር። መላእክትም እነዚህን ነገሮች ለማየት ይጓጓሉ።