ሮም 15:25, 26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 አሁን ግን ቅዱሳንን ለማገልገል* ወደ ኢየሩሳሌም ልጓዝ ነው።+ 26 በመቄዶንያና በአካይያ ያሉት ወንድሞች በኢየሩሳሌም ባሉት ቅዱሳን መካከል ለሚገኙት ድሆች መዋጮ በመስጠት ያላቸውን ነገር በደስታ አካፍለዋልና።+ 1 ቆሮንቶስ 16:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ለቅዱሳን መዋጮ ማሰባሰብን በተመለከተ+ ደግሞ በገላትያ ለሚገኙ ጉባኤዎች የሰጠሁትን መመሪያ መከተል ትችላላችሁ። 2 ቆሮንቶስ 9:1, 2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ለቅዱሳን የሚደረገውን አገልግሎት* በተመለከተ+ ልጽፍላችሁ አያስፈልግም፤ 2 እርዳታ ለመስጠት ፈቃደኛ መሆናችሁን አውቃለሁና፤ በመሆኑም “የአካይያ ወንድሞች ሌሎችን ለመርዳት ለአንድ ዓመት ያህል ዝግጁ ሆነው ሲጠባበቁ ቆይተዋል” ብዬ ለመቄዶንያ ወንድሞች በኩራት ተናግሬአለሁ፤ የእናንተ ቅንዓት ደግሞ አብዛኞቹን አነሳስቷል።
25 አሁን ግን ቅዱሳንን ለማገልገል* ወደ ኢየሩሳሌም ልጓዝ ነው።+ 26 በመቄዶንያና በአካይያ ያሉት ወንድሞች በኢየሩሳሌም ባሉት ቅዱሳን መካከል ለሚገኙት ድሆች መዋጮ በመስጠት ያላቸውን ነገር በደስታ አካፍለዋልና።+
9 ለቅዱሳን የሚደረገውን አገልግሎት* በተመለከተ+ ልጽፍላችሁ አያስፈልግም፤ 2 እርዳታ ለመስጠት ፈቃደኛ መሆናችሁን አውቃለሁና፤ በመሆኑም “የአካይያ ወንድሞች ሌሎችን ለመርዳት ለአንድ ዓመት ያህል ዝግጁ ሆነው ሲጠባበቁ ቆይተዋል” ብዬ ለመቄዶንያ ወንድሞች በኩራት ተናግሬአለሁ፤ የእናንተ ቅንዓት ደግሞ አብዛኞቹን አነሳስቷል።