የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የሐዋርያት ሥራ 8:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 ሳኦልም በጉባኤው ላይ ከፍተኛ ጥቃት ማድረስ ጀመረ። በየቤቱ እየገባ ወንዶችንም ሆነ ሴቶችን ጎትቶ በማውጣት ወህኒ ቤት ያስገባቸው ነበር።+

  • የሐዋርያት ሥራ 9:1, 2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 ሳኦል ግን አሁንም በጌታ ደቀ መዛሙርት ላይ በመዛትና እነሱን ለመግደል ቆርጦ በመነሳት+ ወደ ሊቀ ካህናቱ ሄደ፤ 2 የጌታን መንገድ የሚከተሉትን+ በዚያ የሚያገኛቸውን ወንዶችና ሴቶች ሁሉ አስሮ ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣት በደማስቆ ለሚገኙ ምኩራቦች ደብዳቤ እንዲጽፍለት ጠየቀው።

  • የሐዋርያት ሥራ 22:4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 4 ወንዶችንም ሆነ ሴቶችን በማሰርና ለወህኒ ቤት አሳልፌ በመስጠት የጌታን መንገድ የሚከተሉትን እስከ ሞት ድረስ ስደት አደርስባቸው ነበር፤+

  • የሐዋርያት ሥራ 26:9-11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 እኔ ራሴ የናዝሬቱ ኢየሱስን ስም በተቻለኝ መጠን መቃወም እንዳለብኝ አምን ነበር። 10 ደግሞም በኢየሩሳሌም ያደረግኩት ይህንኑ ነው፤ ከካህናት አለቆችም ሥልጣን ተቀብዬ+ ብዙ ቅዱሳንን ወህኒ ቤት አስገብቻለሁ፤+ እንዲገደሉም የድጋፍ ድምፅ ሰጥቻለሁ። 11 ብዙ ጊዜም በየምኩራቡ እነሱን እየቀጣሁ እምነታቸውን በይፋ እንዲክዱ ለማስገደድ ሞክሬአለሁ፤ በእነሱ ላይ እጅግ ተቆጥቼ በሌሎች ከተሞች ያሉትን እንኳ ሳይቀር እስከ ማሳደድ ደርሻለሁ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ