1 ጢሞቴዎስ 6:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 እንደ እውነቱ ከሆነ ለአምላክ ያደርን+ መሆናችንና ባለን ነገር ረክተን መኖራችን ትልቅ ጥቅም ያስገኛል። 1 ጢሞቴዎስ 6:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ስለዚህ ምግብና ልብስ* ካለን በእነዚህ ነገሮች ረክተን መኖር ይገባናል።+ ዕብራውያን 13:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 አኗኗራችሁ ከገንዘብ ፍቅር ነፃ ይሁን፤+ ባሏችሁ ነገሮች ረክታችሁ ኑሩ።+ እሱ “ፈጽሞ አልተውህም፤ በምንም ዓይነት አልጥልህም” ብሏልና።+